6. ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ፣ ጠጒሯን ትቈረጥ፤ ጠጒሯን መቈረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር መስሎ ከታያት ግን ራሷን ትሸፈን።
7. ወንድ ራሱን መከናነብ የለበትም፤ ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ነውና፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት፤
8. ምክንያቱም ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም።
9. ደግሞም ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም።
10. በዚህ ምክንያት፣ በመላእክትም ምክንያት፣ ሴት በሥልጣን ሥር መሆን የሚያሳይ ምልክት በራሷ ላይ ታድርግ።
11. በጌታ ዘንድ ግን ሴት ያለ ወንድ፣ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም።
12. ሴት ከወንድ እንደ ተገኘች ሁሉ፣ ወንድም ከሴት ይወለዳልና፤ ነገር ግን የሁሉም መገኛ እግዚአብሔር ነው።
13. እስቲ እናንተ ፍረዱ፤ ሴት ራሷን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ይገባታልን?
14. ወንድ ጠጒሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?
15. ሴት ግን ጠጒሯን ብታስረዝም ክብሯ አይደለምን? ረጅም ጠጒር የተሰጣት መጐናጸፊያ እንዲሆናት ነውና።