1 ሳሙኤል 28:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እግዚአብሔር በእኔ የተናገረውን አድርጎአል፤ እግዚአብሔር መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል።

18. ለእግዚአብሔር ስላልታዘዝህ፣ ታላቅ ቊጣውንም በአማሌቃውያን ላይ ስላል ፈጸምህ እግዚአብሔር ዛሬ ይህን አድርጎብሃል።

19. እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”

20. ሳሙኤል ከተናገረው ቃል የተነሣ፣ ሳኦል በፍርሀት ተውጦ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ መሬት ላይ ወደቀ፤ ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ እህል ስላልቀመሰ ጒልበቱ ዝሎ ነበር።

1 ሳሙኤል 28