ዮናስ 2:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እኔም፣ ‘ከፊትህ ጠፋሁ፣ነገር ግን እንደ ገና፣ወደ ቅዱስ መቅደስህ፣እመለከታለሁ’ አልሁ።

5. ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ፤ጥልቁም ከበበኝ፤የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ።

6. ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤አንተ ግን ሕይወቴን ከጒድጓድ አወጣህ።

7. “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ጸሎቴም ወደ አንተ፣ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።

8. “ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፤ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ።

9. እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።”

10. እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፤ ዮናስንም በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።

ዮናስ 2