39. አባቱ ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰለት፤“መኖሪያህከምድር በረከት፣ከላይም ከሰማይ ጠል የራቀ ይሆናል፤
40. በሰይፍ ትኖራለህ፤የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ።አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ወዲያ ትጥላለህ።”
41. አባቱ ያቆብን ስለ መረቀው፣ ዔሳው በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘ፤ በልቡም፣ “ግድ የለም፤ የአባቴ መሞቻው ተቃርቦአል፤ ከልቅሶው በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድላለሁ” ብሎ አሰበ።