32. ሙሴም አለ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘን ይህ ነው፤ ‘ከግብፅ ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ እንድትበሉ የሰጠኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ አንድ ጐሞር መና ወስደህ ለሚመጡት ትውልዶች አቆየው።’ ”
33. ስለዚህ ሙሴ አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ወስደህ አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለሚመጡት ትውልዶች እንዲቆይም እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አስቀምጠው” አለው።
34. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው አሮን፣ መናው ይጠበቅ ዘንድ በምስክሩ ፊት አስቀመጠው።
35. እስራኤላውያን ወደ መኖሪያቸው ምድር እስኪመጡ ድረስ ለአርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ድንበር እስከሚደርሱ ድረስ መና በሉ።
36. አንድ ጎሞር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ነው።