17. ምናልባትም፣ “ይህን ሀብት ያፈራሁት በጒልበቴና በእጄ ብርታት ነው” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።
18. ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለ ሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አስበው።
19. አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ብትረሳና ሌሎችን አማልክት ብትከተል፣ ብታመልክና ለእነርሱ ብትሰግድላቸው በእርግጥ እንደምትጠፉ ዛሬ እመሰክርባችኋለሁ።
20. እግዚአብሔር (ያህዌ) ከፊታችሁ ያሉትን አሕዛብ እንዳጠፋቸው ሁሉ፣ ለአምላካችሁ ለአግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ባለመታዘዛችሁ እናንተም ትጠፋላችሁ።