እስራኤል ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዳነው ሕዝብ፣እንዳንተ ያለ ማን አለ?እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው።ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውንመረማመጃ ታደርጋለህ።