ዘዳግም 33:28-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ስለዚህ እስራኤል ብቻውን በሰላም ይኖራል፤የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣የያዕቆብ ምንጭ የሚነካው የለም።

29. እስራኤል ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዳነው ሕዝብ፣እንዳንተ ያለ ማን አለ?እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው።ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውንመረማመጃ ታደርጋለህ።

ዘዳግም 33