ዘዳግም 27:16-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን! ይበል።

17. “የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

18. “ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፣ የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

19. “በመጻተኛው፣ አባት በሌለውና በመበለቲቱ ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

20. “ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

21. “ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን።ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

22. “የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

23. “ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

24. “በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

25. “ንጹሕን ሰው ለመግደል ጒቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

26. “የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን።”ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ዘዳግም 27