ዘዳግም 10:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) አባቶችህን ስላፈቀረ፣ ወደዳቸው፤ ዛሬም እንደሆነው የእነርሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከአሕዛብ ሁሉ ለይቶ መረጣችሁ።

16. ስለዚህ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙት፤ ከእንግዲህም ወዲያ ዐንገተ ደንዳና አትሁኑ።

17. አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የአማልክት አምላክ (ኤሎሂም)፣ የጌቶች ጌታ (አዶናይ) ታላቅ አምላክ (ኤሎሂም)፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።

18. እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወዳል።

19. ስለዚህ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና መጻተኛን ውደዱ።

20. አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ፍራ፤ አምልከውም፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል።

21. እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ (ኤሎሂም) ነው።

22. አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ ሰባ ነበሩ፤ አሁን ግን አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንደ ሰማይ ከዋክብት አብዝቶሃል።

ዘዳግም 10