ዘካርያስ 11:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል!የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሮአል!

3. የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ክብራቸው ተገፎአልና፤የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!

4. እግዚአብሔር አምላኬ እንዲህ ይላል፤ “ለዕርድ የተለዩትን በጎች አሰማራ፤

5. የገዟቸው ያርዷቸዋል፤ ሳይቀጡም ይቀራሉ፤ የሸጧቸውም፣ ‘እግዚአብሔር ይመስገን፤ ባለጠጋ ሆኛለሁ’ ይላሉ፤ ጠባቂዎቻቸውም እንኳ አይራሩላቸውም።

ዘካርያስ 11