2. “ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሰኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቊርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ’ በላቸው።
3. ደግሞም እንዲህ በላቸው፤ ‘በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የምታቀርቡት መሥዋዕት ይህ ነው፤ አንድ ዓመት የሆናቸውንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በየዕለቱ አቅርቡ።
4. አንዱን ጠቦት ጠዋት ሌላውን ደግሞ ማታ አቅርቡ፤
5. ከዚህም ጋር ተወቅጦ በተጠለለ በሂን አንድ አራተኛ የወይራ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቊርባን አዘጋጁ።
6. ይህም ሽታው ደስ እንዲያሰኝ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቀርብ ምሥዋዕት ሲሆን፣ በሲና ተራራ የተደነገገ መደበኛ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።