ዘኁልቍ 24:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለውን ብቻ ከመናገር በስተቀር ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’

14. እንግዲህ ወደ ሕዝቤ እመለሳለሁ፤ ይሁን እንጂ በሚመጣው ዘመን ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውንና ልንገርህ።”

15. ከዚያም እንዲህ ሲል ንግሩን ጀመረ፤“የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፤የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት ሰው ንግር።

16. የዚያ የአምላክን (ኤሎሂም) ቃል የሚሰማ፣ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣ሁሉን ከሚችለው ራእይ የሚገለጥለት፣መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤

ዘኁልቍ 24