ዕንባቆም 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዝማሬ የቀረበ የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት፤ በሸግዮኖት

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤በእኛ ዘመን አድሳቸው፤በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።

3. እግዚአብሔር ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ሴላክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ውዳሴውም ምድርን ሞላ።

4. ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ጨረር ከእጁ ወጣ፤ኀይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

ዕንባቆም 3