ዕንባቆም 2:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በመጠበቂያ ላይ እቆማለሁ፤በምሽጒ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ምን እንደሚለኝ፣ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ።

2. እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤“በቀላሉ እንዲነበብ፣ራእዩን ጻፈው፤በሰሌዳም ላይ ቅረጸው።

3. ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤እርሱም አይዋሽም፤የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤በርግጥ ይመጣል፤ ከቶም አይዘገይም።

4. “እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤ምኞቱ ቀና አይደለም፤ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል።

ዕንባቆም 2