15. ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ።
16. እነርሱንም ሆነ አባቶቻቸውን በማያውቋቸው ሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”
17. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እንግዲህ፤ አልቃሽ ሴቶች ጥሩ፤ሥልጡን ሙሾ አውራጆች አስመጡ፤
18. እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን።
19. እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቶአል፤ እንዲህም ይላል፤‘ምንኛ ወደቅን!ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው!ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”