ኤርምያስ 6:27-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. “ብረት እንደሚፈተን፣የሕዝቤን መንገድ፣አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

28. ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣ድድር ዐመፀኞች፣ናስና ብረት የሆኑ፣ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።

29. ርሳሱን ለማቅለጥ፣ወናፉ በብርቱ አናፋ፤ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።

30. እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና፣የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።

ኤርምያስ 6