42. ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተማል፤ ያስገመግማል።አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።
43. የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤እጆቹም በድን ሆኑ፤ጭንቀት ይዞታል፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታሟል።
44. አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤የመረጥሁትንም በእርሷ ላይ እሾማለሁ፤እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል?የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?
45. ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደውን፣በባቢሎናውያንም ምድር ላይ ያሰበውን ስሙ፤ከመንጋው ታናናሹ ተጐትቶ ይወሰዳል፤በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።
46. በባቢሎን ውድቀት ድምፅ ትናወጣለች፤ጩኸቷም በሕዝቦች መካከል ያስተጋባል።