11. ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
12. ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ጒዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁናስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ።
13. ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤የችግረኛውን ነፍስ፣ከክፉዎች እጅ ታድጎአልና።
14. የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።
15. “ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል” ብሎ፣ለአባቴ የምሥራች የነገረ፣ደስ ያሰኘውም ሰው የተረገመ ይሁን።
16. ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤በማለዳ ዋይታን፣በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤
17. እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና።
18. ችግርና ሐዘንን ለማየት፣ዘመኔንም በውርደት ለመፈጸም፣ለምን ከማሕፀን ወጣሁ?