ኤርምያስ 2:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ወደ ኪቲም ጠረፍ ተሻገሩና እዩ፤ወደ ቄዳርም ልካችሁ በጥንቃቄ መርምሩ፣እንዲህ ዐይነት ነገር ተደርጎ ያውቅ እንደሆነ ተመልከቱ፤

11. የእውነት አማልክት ባይሆኑም እንኳ፣አማልክቱን የለወጠ ሕዝብ አለን?ሕዝቤ ግን ክብራቸውሠ የሆነውን፣በከንቱ ነገር ለወጡ።

12. ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤”ይላል እግዚአብሔር።

13. “ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፣ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣እኔን ትተዋል፤ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶች፣ለራሳቸው ቈፍረዋል።

ኤርምያስ 2