ኤርምያስ 14:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ድርቅ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2. “ይሁዳ ታለቅሳለች፤ከተሞቿም ይማቅቃሉ፤በምድር ላይ ተቀምጠው ይቈዝማሉ፤ጩኸትም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ይሰማል።

3. መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤እነርሱ ወደ ውሃ ጒድጓዶች ይወርዳሉ፤ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ራሳቸውን ተከናንበው፣ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።

4. በምድሪቱ ዝናብ ስለሌለ፣መሬቱ ተሰነጣጥቆአል፤ገበሬዎችም ዐፍረው፣ራሳቸውን ተከናንበዋል።

5. አንዳች ሣር ባለመኖሩ፣የሜዳ አጋዘን እንኳ፣እንደ ወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።

ኤርምያስ 14