ድምፁን ሲያንጐደጒድ፣ በሰማያት ያሉ ውሆች ይናወጣሉ፤ጉሙን ከምድር ዳር ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤መብረቅን ከዝናብ ጋር ይልካል፤ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።