ኢዮብ 9:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።

29. በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ለምን በከንቱ እለፋለሁ?

30. ሰውነቴን በሳሙና ብታጠብ፣እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣

31. ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።

32. “መልስ እሰጠው ዘንድ፣ እሟገተውም ዘንድ፣እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።

ኢዮብ 9