20. በሸምበቆ ማገዶ ላይ ከተጣደ ድስት እንደሚወጣ እንፋሎት፣ከአፍንጫው ጢስ ይትጐለጐላል።
21. እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል።
22. ብርታት በዐንገቱ ውስጥ አለ፤አሸባሪነትም በፊቱ እመር እመር ይላል።
23. የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ፣በላዩ የጸናና ከቦታው የማይናጋ ነው።
24. ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው።
25. እርሱ በተነሣ ጊዜ፣ ኀያላን ይርዳሉ፤በሚንቀሳቀስበትም ጊዜ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።
26. ጦር፣ ፍላጻ ወይም አንካሴ፣ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።
27. እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።
28. ቀስት አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።
29. ቈመጥ በእርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።
30. የሆዱ ሥር እንደ ሸካራ ገል ነው፤እንደ መውቂያ መሣሪያም በጭቃ ላይ ምልክት ጥሎ ያልፋል።
31. እንደሚፈላ ምንቸት ጥልቁን ያናውጠዋል፤ባሕሩንም እንደ ሽቶ ብልቃጥ ያደርገዋል።
32. ያለፈበትን መንገድ ብሩህ ያደርጋል፤ቀላዩንም ሽበት ያወጣ ያስመስለዋል።
33. ያለ ፍርሀት የተፈጠረ፣እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።
34. ከፍ ያሉትን ሁሉ በንቀት ይመለከታል፤በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።”