ኢዮብ 39:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን?ዋልያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል?

2. የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደሆነ ትቈጥራለህን?የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን?

3. ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ።

4. ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም።

5. “ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው?እስራቱንስ ማን ፈታለት?

ኢዮብ 39