ኢዮብ 27:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤

2. “ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን!ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን!

3. በውስጤ የሕይወት እስትንፋስ፣በአፍንጫዬም ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ እስካለ ድረስ፣

4. ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።

5. እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።

6. ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ አልለቀውምም፤በዘመኔም ሁሉ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።

ኢዮብ 27