ኢዮብ 24:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ሁሉን የሚችል አምላክ ለምን የፍርድ ቀን አይወስንም?እርሱን የሚያውቁትስ ለምን ያን ቀን እንዲያው ይጠባበቃሉ?

2. ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።

3. የድኻ ዐደጉን አህያ ቀምተው ይሄዳሉ፤የመበለቲቱንም በሬ በመያዣነት ይወስዳሉ።

4. ችግረኛውን ከመንገድ ያስወግዳሉ፤የምድሪቱም ድኾች ይሸሸጋሉ።

5. በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች፣ድኾች ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ከበረሓው ምድር ለልጆቻቸው ምግብ ይሻሉ።

ኢዮብ 24