ኢዮብ 23:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።

15. በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።

16. እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።

ኢዮብ 23