14. በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣
15. በዚያን ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤
16. መከራህን ትረሳለህ፤ዐልፎ እንደሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።
17. ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፤ጨለማውም እንደ ንጋት ይሆናል።
18. ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ዙሪያህን ትመለከታለህ፤ በሰላምም ታርፋለህ።
19. ያለ አንዳች ሥጋት ትተኛለህ፤ብዙ ሰዎችም ደጅ ይጠኑሃል።
20. የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለችማምለጫም አያገኙም፤ተስፋቸውም ሞት ብቻ ነው።”