እስራኤላውያን ግን እርም የሆነውን ነገር ለራሳቸው በመውሰድ በደሉ፤ ይህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው አካን የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ስለ ወሰደ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።