ኢያሱ 4:20-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ኢያሱም ከዮርዳኖስ ወንዝ ያወጧቸውን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች በጌልገላ ተከላቸው፤

21. እስራኤላውያንንም እንዲህ አላቸው፤ “ልጆቻችሁ ወደ ፊት፣ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው አባቶቻቸውን ቢጠይቁ፣

22. ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤

ኢያሱ 4