ኢያሱ 15:47-60 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋር፣ ጋዛ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋር።

48. በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ

49. ደና፣ ዳቤር የምትባለው ቂርያትስና

50. ዓናብ፣ ኤሽትሞዓ፣ ዓኒም፣

51. ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

52. አራብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣

53. ያኒም፣ ቤትታጱዋ፣ አፌቃ

54. ሑምጣ፣ ኬብሮን የተባለችው ቂርያትአርባቅና ጺዖር ናቸው፤ እነዚህም ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

55. ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ

56. ኢይዝራኤል፣ ዮቅድዓም፣ ዛኖዋሕ፣

57. ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

58. ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣

59. ማዕራት፣ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ናቸው፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

60. ቂርያትይዓሪም የተባለችው ቂርያ ትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

ኢያሱ 15