39. ለኪሶ፣ ቦጽቃት፣ ዔግሎን፣
40. ከቦን፣ ለሕማስ፣ ኪትሊሽ፣
41. ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው።
42. ልብና፣ ዔትር፣ ዓሻን
43. ይፍታሕ፣ አሽና፣ ንጺብ፣
44. ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው።
45. አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋር፣
46. እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣
47. አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋር፣ ጋዛ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋር።
48. በኰረብታማዋም አገር የሚገኙ ከተሞች ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ሳምር፣ የቲር፣ ሶኮ