ኢዩኤል 2:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በጽዮን መለከትን ንፉ፤በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ፤በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፤እርሱም በደጅ ነው።

2. ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው።የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።

ኢዩኤል 2