ኢዩኤል 1:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እናንት ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤እናንት የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤የዕርሻው መከር ጠፍቶአልና።

12. ወይኑ ደርቆአል፤የበለስ ዛፉም ጠውልጎአል፤ሮማኑ፣ ተምሩና እንኮዩ፣የዕርሻው ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ስለዚህ ደስታ፣ከሰው ልጆች ርቆአል።

13. ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤እናንት በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤የእህል ቊርባኑና የመጠጥ ቊርባኑ፣ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጦአልና።

14. ቅዱስ ጾምን ዐውጁ፤የተቀደሰንም ጉባኤ ጥሩ፤ሽማግሌዎችን ሰብስቡ፤በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ፣ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ጥሩ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።

ኢዩኤል 1