ኢሳይያስ 63:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ይህ ከኤዶም፣ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው?ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው?“በጽድቅ የምናገር፣ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።”

2. መጐናጸፊያህ፣ ለምንበወይን መጭመቂያ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ?

3. “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋር አልነበረም፤በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቶአል፤ልብሴንም በክዬዋለሁ።

4. የበቀል ቀን በልቤ አለ፤የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአል።

5. ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤የገዛ ቊጣዬም አጸናኝ፤

ኢሳይያስ 63