ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ነገር ግን፣ “ደስታዬ በእርሷ” ትባያለሽ፤ምድርሽም፣ “ባለ ባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ምድርሽም ባለ ባል ትሆናለች።