ኢሳይያስ 48:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “የያዕቆብ ቤት ሆይ፤እናንት በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣እናንት በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ!

2. እናንት የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪዎች ነን ብላችሁ ራሳችሁን የምትጠሩ፣በእስራኤል አምላክ የምትታመኑ፣ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው የሚለውን አድምጡ፤

3. የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤እኔም ድንገት ሠራሁ እነርሱም፤ ተፈጸሙ።

ኢሳይያስ 48