ኢሳይያስ 42:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።

2. አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።

3. የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።

4. ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”

ኢሳይያስ 42