ኢሳይያስ 38:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል።ስለ አንተ ታማኝነትም፣አባቶች ለልጆቻቸው ይነግራሉ።

20. እግዚአብሔር ያድነኛል፤ስለዚህ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።

21. ኢሳይያስም፣ “የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳችሁ በዕባጩ ላይ አድርጉለት እርሱም ይፈወሳል” ብሎ ነበር።

22. ሕዝቅያስም፣ “ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድን ነው?” ብሎ ነበር።

ኢሳይያስ 38