1. ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣በፈረሶች ለሚታመኑ፣በሠረገሎቻቸው ብዛት፣በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!
2. እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ቃሉን አያጥፍም።በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።
3. ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ተረጂውም ይወድቃል፤ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
4. እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦልየሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ብዙ እረኞችተጠራርተው ሲመጡበት፣ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።