ኢሳይያስ 29:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣አርኤል፣ አርኤል ወዮልዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።

2. ነገር ግን አርኤልን እከባለሁ፤ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።

3. በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በቅጥር እከብሻለሁ፤የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።

4. ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ንግግርሽ ከትቢያ እየተጒተመተመ ይወጣል፤ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።

5. ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣መንጋ ጨካኞችም በነፋስ እንደሚነጻገለባ ይሆናሉ።ድንገት ሳይታሰብም፣

6. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በነጐድጓድ፣ በምድር መናወጥና በታላቅ ድምፅ፣በዐውሎ ነፋስና በኀይለኛ ሞገድ ፈጽሞ በሚባላም የእሳት ነበልባል ይመጣል።

7. አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከባት፣እንደ ሕልምበሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።

8. የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።

9. ነሁሉሉ፤ ተደነቁም፤ተጨፈኑ፤ እስከ ወዲያኛውም ታውራችሁ ቅሩ፤በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ስከሩ፤በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳገዱ።

ኢሳይያስ 29