9. ሰው ዝቅ ብሎአል፤የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።
10. ከእግዚአብሔር አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ወደ ዐለቶች ሂድ፤በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።
11. የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።
12. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣የተኵራራውን በሙሉየሚያዋርድበት ቀን አለው።
13. ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣
14. ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ከፍ ያለው ኰረብታ ሁሉ፣
15. ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፣የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣
16. የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።
17. የሰው እብሪት ይዋረዳል፤የሰውም ኵራት ይወድቃል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤