1. የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤
2. በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።
3. ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤በጐዳናውም እንሄዳለን።”ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
4. እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል።እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።
5. እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።