ኢሳይያስ 17:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤“እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።

2. የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም የለም።

3. የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤የሶርያም ቅሬታእንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

4. “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፤የሰውነቱም ውፍረት ይሟሽሻል።

5. አጫጅ የቆመውን ሰብል ሰብስቦ፣ዛላውንም በክንዱ እንደሚያጭድ፣ይህም በራፋይም ሸለቆእንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።

ኢሳይያስ 17