3. እግዚአብሔር ከሥቃይህ፣ ከመከራህና ከጽኑ ባርነትህ ባሳረፈህ ቀን፣
4. በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ጨቋኙ እንዴት አበቃለት!አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!
5. እግዚአብሔር የክፉዎችን ዘንግ፣የገዦችንም በትረ መንግሥት ሰብሮአል፤
6. ሕዝቦችን በማያቋርጥ ቍጣ የመታውን፣ያለ ርኅራኄ እያሳደደየቀጠቀጠውን ሰብሮአል።
7. ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።
8. ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ደስ ብሎአቸው፣“አንተም ወደቅህ፤ዕንጨት ቈራጭምመጥረቢያ አላነሣብንምቃ አሉ።
9. በመጣህ ጊዜሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታትከዙፋናቸው አውርዳለች።
10. እነርሱ ሁሉ ይመልሱልሃል፤እንዲህም ይሉሃል፤“አንተም እንደ እኛ ደከምህ፤እንደ እኛም ሆንህ።”
11. ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁወደ ሲኦል ወረደ፤ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ።
12. አንተ የንጋት ልጅ፣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፤እንዴት ከሰማይ ወደቅአንተ ቀድሞ መንግሥታትን ያዋረድህ፤እንዴት ወደ ምድር ተጣልህ!