ኢሳይያስ 14:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቦአል፤ማንስ ያግደዋል?እጁም ተዘርግቶአል?ማንስ ይመልሰዋል?

28. ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤

29. “እናንት ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።

30. ከድኻም ድኻ የሆኑት መሰማሪያ ያገኛሉ፤ችግረኞችም ተዝናንተው ይተኛሉ፤ሥርህን ግን በራብ እገድላለሁ፤ትሩፋንህንም እፈጃለሁ።

31. በር ሆይ፣ ዋይ በል፤ ከተማ ሆይ ጩኽ፣ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።

ኢሳይያስ 14