አሞጽ 6:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

13. እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፣“ቃርናይምን በራሳችን ብርታት ይዘናል” የምትሉ፣

14. ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እነሆ፤ እኔ ከሐማት መግቢያ እስከ ዓረባ ሸለቆ ድረስ፣የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ፣ በእናንተላይ አስነሣለሁ።”

አሞጽ 6