አሞጽ 1:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ድንበሩን ለማስፋት፣የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀዶአልና።

14. በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ምሽጎቿን እንዲበላ፣በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።

15. ንጉሥዋ ከሹማምንቱ ጋር፣በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል፣”ይላል እግዚአብሔር።

አሞጽ 1