ሰቆቃወ 5:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።

19. አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ለዘላለም ትገዛለህ፤ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

20. ስለ ምን ፈጽመህ ትረሳናለህ?ስለምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?

21. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፤

22. ፈጽመህ ካልጣልኸን፣ከመጠን በላይ ካልተቈጣኸን።

ሰቆቃወ 5